Monday, May 13, 2013
Friday, February 1, 2013
አምልኮ ምንድን ነው?
- "ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።"ዮሃን4፡23-24
- አምልኮ እራሳችን አዋርደን በፊቱ በመንፋስ እና በእውነት መስገድ ነው ። ሌላው እኛ አምለኮ በለን የምንለው የዘማሬ አይነት 1 ክፍል ብቻ ነው ቃሉንም ማጥናት፤ መጸለይም፤ ኑሮአችንም ሁሉ በመንፋስ ስንመላለስ እሱን ከፍ አድርገን እኛ ዝቅ ብለን መገዛት አምልኮነው
ስለዚህ ኢያሱ "እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን" እናመልካለን ሲል ወይም ሰለሞን ሌሎችን አማልክት አመለከ ወዘተ ሲል መጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር ዘመሩ ወይም እኛ በአሁኑ ዘመን እንደሚገባን "የአምልኮ ፕሮግራም" ያካሂዱ ነበር ማለት አይደለም። ነገር ግን አምላካችን ነው የሚሉት አምላክ ያዘዛቸውን ያደርጉና ይታዘዙ ነበር ማለት ነው።
ስለዚህም ነው አንድ ሰው እግዚአብሔርን አምላኪ (ተከታይ ወይም የእግዚአብሔር ታዛዥ) መሆኑና አለመሆኑ በኑሮው ነው የሚታወቀው። በእስራኤል ንጉሶች እግዚአብሔርን ያመልኩ ወይም አያመልኩ እንደነበር ስለ እያንዳንዱ ማለት ይችላል በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እናገኛለን። አመለኩ የሚባሉት ንጉሶች ወይም ሰዎች ለምሳሌ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሰንበትን ማክበር፣ አትብሉ ያለውን አለመብላት፣ እርሱ እንደፈለገ ጽድቅ ፍትህንና ፍርድን ማድረግ፣ እርሱ ያዘዛቸውን በዓላትን ማክበር፣ መስዋእቶችን ወዘተ ማድረግ፣ ለሌሎች አማልክት አለመሰዋት ወዘተ የሚባሉት ነገሮች በኑሮአቸው ስለሚታዩ ሰዎች ከኑሮአቸው አይተው እግዚአብሔርን ያመልኩ (ይከተሉ) እንደሆነና እንዳልሆነ ያውቁ ነበር።
በአንጻሩ ደግሞ እንደዚህንና የመሳሰሉትን በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ያደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ነገሮች የማያደርጉ በተቃራኒው ግን ክፋትን የሚያደርጉ፣ ድሆችን የሚያስጨንቁ፣ ፍትህን የማይወዱ፣ ለሌሎች አማልክት የሚሰው ወዘተ ደግሞ እግዚአብሔርን እንደማያመልኩ ነበር የሚቆጠሩት።
ስለዚህ አምልኮ የሚለው ቃል አንተ የማነህ የሚለውን የሚያመለክት ነው። ማንን ታመልካለህ ማለት የማንን ፈቃድ ነው በህይወትህ እየታዘዝክ ያለኸው ማለት ነው።
ስለዚህ አምልኮ በመሰረቱ ከዝማሬ ወይም በቤተመቅደስና በጉባኤ ከሚደረጉ ሃማኖታዊ ስርዓቶች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በእርግጥ ነው እግዚአብሔርን በኑሮአቸው የሚታዘዙ ሰዎች የከንፈሮቻቸውን መስዋእት በዝማሬ ቢያቀርቡ መልካም ነው። ሆኖም ግን በቤተመቅደስና በጉባዬ የሚደረጉ አምልኮዎች እግዚአብሔርን በህይወት መታዘዝ ከሌለበት እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈውና የማይቀበለው ነገር እንደሆነ ብዙ ጊዜ በነብያቱ ተነግሮአል። እንዲያውም በብሉይ ኪዳን ቤተመቅደሱ በእንዲህ ያሉት ሰዎች ሲሞላ መጽሐፍ ቅዱስ በኤርምያስ 7 ላይም ይሁን በጌታ በኢየሱስ እንደሚናገረው ቤተመቅደሱን "የወንበዴዎች ወይም የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት" ነው የሚለው። የወንበዴዎች ዋሻ የሚባለው በዛን ዘመን ወንበዴዎች ወይም ወንጀለኞች ከገደሉና ሕገ ወጥ ድርጊት ካደረጉ በኋላ መንግስት እንዳይቀጣቸው የሚደበቁባቸው በተራሮች ወገብ ላይ የሚቆፈሩ ከፍርድ ማምለጫና መሸሸጊያ ቦታዎች ናቸው። ስለዚህ በህይወታቸው ክፉ እያደረጉና እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህይወት እየኖሩ በቤተመቅደስና በጉባኤ በሚደረግ "አምልኮ" ሊሸሸጉና ሊታመኑ ለሚፈልጉ በኤርምያስ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው። ኤርምያስም እንዳስጠነቀቀው የታመኑበት መሸሸጊያ ቤተመቅደስ በባቢሎን ተቃጠለ፣ ተዘረፈና ፈረሰ። ስለዚህ አምልኮ በዋናነት በፕሮግራም ወይም በጉባኤ የሚደረግ ነገር አይደለም።
0 ድምጾች

©
ሔኖክ
ሰለሞን
ጥር
24፣ 2005
አዲስ
አበባ
Friday, February 1, 2013
The body is a unit, though it is made up of many
parts; and though all its parts are many, they form one body. So it is
with Christ. For we were all baptized by one Spirit into one
body--whether Jews or Greeks, slave or free--and we were all given the
one Spirit to drink.
1 Corinthians 12:12-13 (Read all of 1 Corinthians 12)
New International Version
New International Version
Subscribe to:
Posts (Atom)