መዝሙረ ዳዊት 23 | |||
0 | የዳዊት መዝሙር። | ||
1 | እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። | ||
2 | በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። | ||
3 | ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። | ||
4 | በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። | ||
5 | በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። | ||
6 | ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። |
No comments:
Post a Comment